=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
በአል-ቡሐሪ አል-አደብ አል-ሙፍረድ ውስጥ እንደተዘገበው
መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ.) ወንድሞቻችሁ ጋር አትነታረኩ ፣ አትጨቃጨቁ ከእርሱም ጋር ቅጥ ባለፈ መልኩ አትቀላለዱ፤ የምታፈርሱት የሆነን ቃልኪዳንም አትግቡ ብለዋል።
ንትርክ ወደ በለጠ አለመግባባት እና ድርቅና ያመራል፤ ለኢብሊስም ክፍት ቦታ ይፈጥራል። አብዛሃኛውን ጊዜ ስሜትን የሚጐዳ የሆነ ቀልድ ጥላቻ እና ክብር ማጣትን ያስከትላል። ቃልኪዳንን ማፍረስ ሰዎችን ሲያበሳጭ በመካከላቸው የነበረውንም ፍቅር ጥላሸት ይቀባዋል። የሚያቆራርጥን ነገር ላለመናገር ማፈግፈግን መማር ይኖርብናል። አንዳንዴም ችግሩ የተሻለ እውቀት ባለው ሰው እስኪፈታ ድረስ "ላለመስማማት መስማማት" ይኖርብናል።
የተለያዩ የአካል እንቅስቃሴዎች እና በነሱ የሚደረጉ ምልክቶች ለምሳሌ ጣትን መቀሰር ፣ ጥርስን መንከስ ወ.ዘ.ተ አለመግባባትን እና ጥላቻን ስለ ሚፈጥሩ ተያቸው፤ ከዚህም ልትርቂ ይገባል።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|